Connect with us

Uncategorized

ትግራይ ላይ የሚካሄደው ጦርነት ብ ሌላ ኢትዮጵያዊት ዓይን (ክፍል 2)

መቀሌም “safe” እንዳልሆነ ውስጣችን እየነገረን ነበር። የምንገባበት ጥግ አጣን። አንድ ጓደኛዬ እሷ ጋር መውለድ እንደምችል ስለነገረችን ለቤተሰቦቿ የተወሰነ ብር ሰጠናቸው። ከስራ ሳንናገር ስለወጣን ባለቤቴ እረፍት ለመሙላት ልመለስ አለኝ። ውስጤን በጣም ከፋ፤ የማንገናኝም መሰለኝ፤ ተደብቄ ማልቀስ ጀመርኩ።

Published

on


የፀሐፊዋ መገቢያ (ስሟ ሊገለፅ ኣልፈለገችም)፦ ትግራይ ውስጥ ለ1 አመት ከ8ወር ኖሬአለሁ። ጦርነቱ ከመታወጁ በፊት ህይወት መልካም ነበር። ማንም ሰው ይሄ እንዲገጥመው አልመኝም። ጦርነቱ ከተጀመረ ለ20 ቀናት የገፈቱ ቀማሽ የችግሩም ተቋዳሽ ነበርኩ።


መቀሌም “safe” እንዳልሆነ ውስጣችን እየነገረን ነበር። የምንገባበት ጥግ አጣን። አንድ ጓደኛዬ እሷ ጋር መውለድ እንደምችል ስለነገረችን ለቤተሰቦቿ የተወሰነ ብር ሰጠናቸው። ከስራ ሳንናገር ስለወጣን ባለቤቴ እረፍት ለመሙላት ልመለስ አለኝ። ውስጤን በጣም ከፋ፤ የማንገናኝም መሰለኝ፤ ተደብቄ ማልቀስ ጀመርኩ።

የዛን ሰአት የነበርነው ከጓደኛው ቤት ነበር። ያው ገንዘብ ስለሌለ ጓደኛው ፊቱን ማጥቆር ጀምሮ ነበር። ከዛም ባለቤቴ ወደ መናኸሪያ ሲሄድ ሻንጣ ሚጎትቱ ሰዎች ያገኛል። ከየት ነው ምትመጡት ሲላቸው ግማሹ ከምኾኒ ግማሹ ከማይጨው ግማሹ ከሁመራ ይሉታል። ከቻልክ ወደ ገጠር መሄድ ነው ይሉታል። ተመልሶ መጣ። ሳየው የተሰማኝ ደስታ ልዩ ነበር። አባቴ እንኳን መጣህ አልኩት። እሱ ግን ፊቱ ልክ አልነበረም። እየተጨዋወትን በመሀል በነገራችን ላይ መናኸርያ ሆኜ አዲስ አበባ እያሉ እየጠሩ ነበር አለኝ። ልቤ ቀጥ አለ ፤ ግን መወሰን አለብኝ። እጃችን ያለው ብር እያለቀ ነው። የመጀመሪያ ልጄን እናቴ ጋር መውለድ አለብኝ። ስለ ልጅ እንክብካቤ የማውቀው አንዳች ነገር የለም። እንሂድ አልኩት ፍርጥም ብዬ ። ከሰአት ሄድን ፤ ነገ ጠዋት 2 ሰአት ላይ አፋር የሚገባ መኪና አለ አሉን። እቃችንን ከጓደኛው ቤት ወሰድን እና ሆቴል ያዝን። ለሊቱን እንቅልፍ ሚባል በአይኔ አልዞረም። ድርሳነ ሚካኤል ካነበብኩ በሁዋላ ጌታ ሞገስ እንዲሆነን ፀለይኩ።

እንዳይነጋ የለም ነጋ። መናኸሪያ ደረስን። ደላላው መኪናው ጋር አደረሰን። ሚኒባሱ ውስጥ ካለው 12 ሰው 6 ኤርትራውያን ሲሆኑ አንድ ቄስ ፣ 1 የጎንደርልጅ፣ 1 አፋር ምትሰራ ሴት ከሁለት ህፃናት ጋር እና 1 የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪ (ብር ስለሌላት አዋጥተን ምንወስዳት) ነበርን። መኪናው ሊነሳ ሲል ሾፌሩ ኬላ ላይ ስንደርስ ከትግራይ ክልል መታወቂያ ውጪ እንደሚያስፈልግ መናገር ጀመረ። ደነገጥን ፤ እኔ አማራ ስሆን ትውልዴ ኦሮሚያ ባለቤቴ ደግሞ ትግራዋይ ነው።ባለቤቴ አፋር ላይ ከመለሱኝ አንቺ ትሄጃለሽ እኔ እመለሳለሁ ፤ ከሰመራ በplane ትሄጃለሽ አለኝ። እኔ እና ባለቤቴ ተለያይተን አናውቅም ፤ እሱን ብዬ ነው የመጣሁት ፤ እሱን ብዬ ብዙ ዋጋ ከፍያለው ፤ እሱም እኔን ብሎ ብዙ ዋጋ ከፍሏል። አፋር ላይ ከመለሱክ አብረን እንመለሳለን አልኩት። ከልቤ ነበር።

በመቀጠል ሾፌሩ እስከ አፋር ኬላ እንደማያደርሰን ነገር ግን ኔትወርክ (ከተሳሳትኩ አርሙኝ) የሚባል ቦታ እንደሚያደርሰን ከዛ በሁዋላ እስከ አፋር ኬላ በእግር እንደምንሄድ ነገረን። የእግር መንገዱ የአንድ ሰአት ተኩል እንደሚሆን ነገረን። በተጨማሪም ወደ አብአላ የሚባለው የአፋር ከተማ እንደምንሄድ እንጂ ወደ አ.አ እንደምንሄድ እንዳንናገር አስጠነቀቅን።እኔ በበኩሌ ያን ያህል አላስጨነቀኝም ነበር። ምክንያቱ ደግሞ የበለጠው የባለቤቴ ጉዳይ ነበር ያሳሰበኝ።

መንገድ ጀመርን። ድርሳነ ሚካኤል አሁንም አነበብኩ። ባለቤቴም እንዲያነብ አደረኩ። ሾፌሩ የነገረን ቦታ ስንደርስ ተፈተሽን። ጎረምሶቹ ወደ ፊት ቀደሙ። እኛ እና ህፃናት የያዙት ሴቶች ወደ ሁዋላ ቀረን። የፀሀዩ ንዳድ ከምገልፀው በላይ ነው። ቁርስ አልበላንም።የውሀ ጥማት አለ። የያዝነውን ኮካ እና ብስኩት እኔ እና ህፃናቱ በላነው። በዛ ላይ በእርግዝናው ምክንያት ሽንቴ ቶሎ ቶሎ ነው ሚመጣው። እና ደግሞ ወደ ታች እየተጫነኝ ነበር። ውስጤ በጣም እየፈራ ነበር፤ እዚህ በረሀ ላይ ምጤ ቢመጣ ምንድነው ምሆነው እያልኩኝ ከራሴ ጋር አወራ ነበር። የተወሰነ መንገድ እንደሄድን የትግራይ ልዩ ሀይል አስቆሙን። አፋር ኬላ ላይ ከትግራይ ክልል ሰው እንደማይቀበሉ እነሱም እንዳታሶጡ መባላቸውን ነገሩን ሻንጣችንን መሬት ላይ አስቀምጠን ቁጭ አልን። አንድ 20 ወይም 30 ደቂቃ እንደተቀመጥን አንድ የእነሱ አለቃ መጣ እና ይሂዱ ብሎ ነገራቸው። መንገዳችንን ቀጠልን። አስፓልቱ ማለቂያ የለውም። አቋራጭ ብለን የገባንበት መንገድ እንኳንስ ለነብሰ ጡር ለብርቱ ጎረምሳ እንኳን ይፈትናል። የቁልቁለት መንገድ ይበዛዋል። ድንጋያማ የሚያንሸራትት ነበር። በመጨረሻም የአፋር ኬላ አብአላ ደረስን።

Continue Reading
Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Copyright © TGHAT